Posts

የመጥምቀ መለኮተ ቅዱስ ዮሐንስ ሕይወትና አገልግሎት ክፍል አንድ

በቤተ ክርስቲያናችን ከመስከረም 1 እስከ 7 ያለው ጊዜ   ዘመነ ዮሐንስ ይባላል፤ ሳምንቱ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ሕይወቱ፣ትምህርቱና ምስክርነቱ የሚታሰቡበት ነው። የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ልደትና ዕድገት ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ምዕራፍ አንድ ላይ « በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱ ኤልሳቤጥም ከአሮን ነገድ ነበረች። ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም። » በማለት የቅዱስ ዮሐንስን እናትና አባት ያስተዋውቀናል / ሉቃ .1÷5-7/ ። የአብያ ምድብ በመጽሐፈ ዜና መዋዕል ምዕራፍ 23 እና 24 ላይ ንጉሠ እስራኤል ዳዊት ሸምግሎ መንግሥቱን ለልጁ ለሰሎሞን ሲያስረክብ በዘመኑ የነበሩትን ካህናት / ሌዋውያን እና የአሮን ልጆች / አስቆጥሮ በዕጣ በተለያዩ የአገልግሎት ምደቦች በየነገዳቸው መድቦ በዕጣ የአገልግሎት መርሃ ግብር አውጥቶላቸው ነበር። የአብያ የካህናት ምድብ ከእነዚህ አንዱ ነበር። ብሥራተ ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ ካህኑ ዘካርያስና ቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን ዘወትር በጸሎት ይጠይቁ ነበር። አንድ ቀን ዘካርያስ እንደ ብሉይ ኪዳኑ ሥርዓት / ዘጸ .3 ዐ ÷6-8/ ወደ ቤተ መቅድስ ገብቶ ዕጣን የማጠን ተራ ደርሶት / ዕጣ ወጥቶለት / ወደ ቤተመቅደስ ሲገባ መልአከ እግዚአብሔር ከዕጣን መሠዊያው / ከዕጣን መሥዋዕት